top of page

ውሎዬ- የኪ ድልድይ

በጥንታዊቷ የወደብ ከተማ ቦልቲሞር ውሎዬ ካየኋቸው ሦስት አጫጭር ነገሮች ላካልፍላችሁ ወሰንኩ። የመጀመሪያው ትልቁ  የኪ ድልድይ ነው። ከ43 ዓመታት በፊት የተገነባው ይህ ድልድይ  1.6 ማይሎች ይረዝማል። መታሰቢያነቱ ለፍራንሲስ ስኮት ኪ ነው። እርሱ ደግሞ የአሜሪካ ብሔራዊ መዝሙር ደራሲ ነው። 

መዝግብት እንደሚነግሩን ኪ በሙያው ጠበቃ ሲሆን በዚያ ወሳኝ ወቅት ቦልቲሞር የመጣው ዶ/ር ዊልያም ቢንስ የተባለን ሰው ተደራድሮ ከእሥር ቤት ለማስፈታት ነበር።  ወገኖቹ እንግሊዞችን በመከቱበት ጦርነት ስፋቱ 5.2 በ7.6 ሜትር የሆነ ባንዲራ በማክሔንሪ ምሽግ ላይ ይውለበለብ ነበር። በበነጋው 9.1 በ12.8 ሜትር የሆነና ከዚያም የገዘፈ ባንዲራ ተሰቅሎ መታየቱ የአሜሪካ ሠራዊት የእንግሊዝን ወራሪ ኃይል ገትሮ እንዳቆመው ድል እንዳደረገም ጭምር አበሰረ። ያንን ዐይቶ የተነቃቃው ፍራንሲስ ስኮት ኪ “የማክሔንሪ ምሽግ ምክቶሽ” የሚል ግጥም ጻፈ።   ይህ ግጥም ኋላ ርዕሱ “በከዋክብት ያሸበረቀው አርማ” በሚል ተቀይሮ የአሜሪካ ብሔራዊ መዝሙር ሆኗል።  አሁንም ነው። ምክንያቱም አሜሪካውያኑ መሪ በተቀየረ ቁጥር መዝሙር አይቀይሩም። አሁን በዚያው ምሽግ ውስጥ ሐውልት አቁመውለታል። ይልቁንም ይህን በውኃ ላይ የተዘረጋ ግዙፍ አረግራጊ ድልድይ በስሙ ሰይመውለታል።

28 views0 comments

Comments


bottom of page